አካታች የትምህርት ስርዐት ለተሻለ ነገ

by centerfordemocraticsociety

ሊገባደድ ቀናቶች በቀሩት 2014 ዓ.ም የቀጣይ አመት የትምህርት ዘመን ምዝገባ በመካሄድ ላይ ይገኛል፤
ከዚሀም ጋር ተያይዞ ብዙ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች አሉ። ትምህርት ለግለሰብ እድገት እና ለሌሎች
መብቶች መሸጋገሪያ በመሆኑ ለሁሉም ተደራሽ መሆን አለበት። ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ የትምህርት መብት
የግለሰብን ነፃነት፣ ማብቃት፣ ሰብአዊ ልማት፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መብቶችን ያበረታታል። የመማር
መብትን ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ ለማድረግ በቅድሚያ ማንንም በማይተው መልኩ የተቀየሰ፣ የሚደግፍ እና
የሚተገበር ሥርዓት መኖር አለበት።


በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ማህበረሰብ 18% የሚሆንው አካል ጉዳተኛ እንደሆነ ይገመታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ
በሀገሪቷ ውስጥ የሚገኙት መሰረተ ልማቶች ፣ ሕንፃዎች እንዲሁም የሚሰጡ አገልግሎቶች አካል ጉዳተኞችን
ያማከሉ አይደሉም። ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት ስለ አካል ጉዳተኛ ሰዎች መብት የሚተነትኑ አለም አቀፍ ይሁን
የሀገር ውስጥ ህጎች የአካል ጉዳትኞችን እኩል ተጠቃሚነት መብት ይደነግጋሉ፤ ከነዚህም መካክል ጥራቱን
የጠበቀ፣ ተደራሽ የሆነ የትምህርት አገልግሎት የማግኘት መብት ይጠቀሳል።


በ2004/2012 ወደ ትግበራ የገባው አካል ጉዳተኞች ላይ ያተኮርው ብሔራዊ ፕላን የተለያዩ ቅድሚያ
የሚሰጣቸው ዘርፎች ያስቀምጣል፤ ከነዚህም ዘርፎች አንዱ የትምህርት ሴክተር ነው። በቂ ድጋፍ ከተገኘ ብዙ
አካል ጉዳተኛ ልጆች በመደበኛ ትምህርት ቤቶች እና ክፍሎች መማር እንደሚችሉ እቅዱ ያረጋግጣል። ፕላኑን
ተከትሎ የወጣው አካታች የትምህርት ስትራቴጂ ይህንኑ ያጠናከረ ሲሆን በመሬት ላይ የሚታየውን አካል ጉዳተኛ
ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳይቀመጡ እንቅፋት ናቸው ያላቸውን ነጥቦች ላይ የመፍትሔ ሀሳብ
አስቀምጧል። የግንዛቤ ማነስ፣ የመማሪያ አካባቢዎች ምቹ እና ተደራሽ አለመሆን እንዲሁም የመማሪያ
ቁሳቁስ እጥረት ላይ የመፍትሔ ሃሳቦችን ያስቀምጣል። ከመፍትሔ ሃሳቦቹ መካከል በየደረጃው የሚገኙ
የትምህርት ቢሮዎች በማህበረሰቡ እንዲሁም ከትምህርት ቤት አካላት ጋር የግንዛብ ማስጨበጫ ስራዎች
እንዲሰሩ ይደነግጋል።


ስትራቴጂው በትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ መገልገያዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆኑ ያስቅምጣሉ፤
በዚህም ባለ ብዙ ፎቅ ሕንፃዎችን የሚገነቡ ትምህርት ቤተች የተሻሻለ መወጣጫ መገንባት፣ እስከዚያው ግን
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሚማሩበትን ክፍሎች መሬት ላይ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ይህ በእንዲህ
እንዳለ በተለያዩ የትምህርት እርከኖች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ምዝገባ ቁጥር በጣም አናሳ ነው፤ ይህም
በየደረጃው ከመጀመሪያ ደረጃ ወደ ከፍተኛ ትምህርት እየቀነሰ ይሄዳል። ለዚህም የማህበረሰቡ አካል ጉዳተኛን ትምህርት ቤት ያልመላክ ፍላጎት፣ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምቹ ሁኔታ አለመኖር እንዲሁም በዘርፉ የሰለጠነ ብቁ ባለሙያ አለመኖር እንደ ምክንያት ይነሳሉ።


ይህን ችግር ክመሰረቱ ለመቅረፍ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የበኩሉን አስተዋፆ ሊያደርግ ይገባል። መንግስት
በስራ ላይ ያለውን አካታች የትምህርት ስትራቴጂ ትግበራ ምን እንደሚመስል፣ በምን ያህል ደረጃ እየተተገበረ
እንደሆነ ክትትል ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሙያዊም ይሁን የቁሳቁስ ድጋፍ ለመስጠት የተደራጁ
በየደረጃው የሚገኙ ተቋማትን አቅም ማጎልበት ይጠበቅበታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ የሲቪል
ማህበራት የማህበረሰቡን ንቃተ-ህሊና ለመጨመር የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት
ማስተማር ፤ ትምህርት ቤቶች አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ብቁ የሚሆኑበትን አቅም
በመገንባት የበኩላቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

አካል ጉዳተኛን ማስተማር የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍይዳ ከመኖሩ በዘለለ ሰብአዊ
መብታቸውን ማክበር ስለሆነ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። ጊዜው የ2015 የትምህርት ዘመን ምዝገባ
የሚካሄድበት በመሆኑ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እኩል የትምህርት ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን መንገዶች
ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

Dureti Hussen!

You may also like

2 comments

Avatar
Kemal August 26, 2022 - 5:51 pm

አካል ጉዳተኛ መሆን እንደ ፈጣሪ እርግማን የሚቆጠርበት አከባቢ እስከአሁን አለ። አንድ ልጅ አካለ ስንኩል ሆኖ ስዎለድ ከቤት እንዳይወጣ ቤት ውስጥ የምታገትበት ሁኔታዎች አልፎ አልፎ ይመለከታሉ። የአመለካከት ችግር መቀረፍ አለበት። አከል ጉዳተኛ ልጆችን እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም አካላት መረባረብን ይጠይቃል።

Reply
Avatar
Derara Ansha October 25, 2022 - 1:49 pm

Thanks Dureti for the wonderful piece. Stereotypes and discriminations against physical disabilities are by no means acceptable!! Education sector, as an institution with the task of shaping generations, must rectify the misunderstandings imbedded in the society.

Reply

Leave a Comment